//ptewarin.net/afu.php?zoneid=3393779

Metsihafe Kidase (Ethiopian Liturgy መጽሐፈ ቅዳሴ)ቅዳሴ 

በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡  ከጸሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሞልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡

፩. የቁርባን መስዋዕት፤ በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ውስጥ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ፀሎት ነው ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል፡፡

፪. የከንፈር መስዋዕት፤ ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡

፫. የመብራት መስዋዕት፤ በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጦፍ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚሰጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ይህውም ጌታችን ጨላመ ለሆነ ዓለም ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡

፬. የዕጣን መስዋዕት፤ የዕጣን ፀሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ በደሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡

፭. የሰውነት መስዋዕትነት፤ በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡

ይህ የፀሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል።
፩. የዝግጅት ክፍል
፪. የንባብና የትምህርት ክፍል
፫. ፍሬ ቅዳሴ እዚህ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ ናቸው። እነዚህም፤
፫.፩. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
፫.፪. ቅዳሴ እግዚእ
፫.፫. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
፫.፬. ቅዳሴ ማርያም
፫.፭. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
፫.፮. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
፫.፯. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
፫.፰. ቅዳሴ ባስልዮስ
፫.፱. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ
፫.፲. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
፫.፲፩. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
፫.፲፪. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
፫.፲፫. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
፫.፲፬. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ

ቅዳሴ የምስጋና ሁሉ መደምደሚያ (ማሰሪያ) በመሆኑ እያንዳንዳችን በቤተክርስቲያን ተገኝተን የጸሎቱ ተሳታፊ በመሆን ለእኛ ኃጢአት በቀራንዮ የተሰቀለውን ክርስቶስን ሥጋውና ደሙን ልንቀበልና የክብሩ ወራሾች ልንሆን ይገባል።  ሥጋውና ደሙ የሚፈተተው ለሕጻናትና ሽማግሎች ብቻ ሳይሆን ከ40 እና ከ80 ቀን ጀምሮ ከመንፈስ ቅዱስ ልጅነት ላገኙ በሁሉም እድሜ ክልል ላሉ ነው። 

ስለዚህ ለሠራነው ኃጢአት ንስሐ እየገባን ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ጸሎተ ቅዳሴው ከመጀምሩ በፊት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት በሥርዐተ ቅዳሴው እና በፍሬ ቅዳሴው የሚነበቡትን ምስጢራት ልናስተውል ልንረዳ ይገባል።  በምናስቀድስበትም ጊዜ ከመሰቀሉ በፊት በዕለተ ሓሙስ የሠራልንን ሥርዐት እንዲሁም ለእኛ ለሰው ልጆች በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ ተሰቅሎ ሥጋውን የቆረሰልን፣ ደሙን ያፈሰ ሰልንን መሆኑን እያሰብን የሠራነውንም ኃጢአት እንዲያስተሰርይልን ሊሆን ይገባል። 
 
ይህ መተግበሪያ እነዚህን የቅዳሴ ክፍሎች በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ) የያዘ ሲሆን የተወሰኑ ክፍሎችንም በትግርኛ አካቷል።


The Liturgy

Sacred liturgy is the very heart of Ethiopian Orthodox worship. All the various kinds and types of Orthodox prayer and ritual cluster around the Sacrifice of the Mass which was instituted by the Lord the same night in which He was betrayed (1 Cor.11: 23-25).

The Ethiopian Liturgy is divided into two parts, the introductory part called Ordo Communis and the Eucharistic part called Anaphora. The Anaphora is the more solemn portion of the Liturgy, the central point of which is the great Oblation. It commences with the words “Sursum Corda”, or with their equivalents, which occur in all Liturgies, and includes the rest of the services to the end.

The Anaphoras are officially fourteen, the basic one in normal use being that of the Twelve Apostles. In the some ancient monasteries about six other Anaphoras are used. The Ethiopic Liturgy was the first to be published of all the Oriental Liturgies. It was printed at Rome in 1548.


Official Anaphoras:
1) Anaphora of the Apostles
2) Anaphora of our Lord Jesus Christ
3) Anaphora of our Lady Mary
4) Anaphora of St. John Chrysostom
5) Anaphora of St. Dioscorus
6) Anaphora of St. John the Evangelist
7) Anaphora of St. Gregory the Armenian
8) Anaphora of the 318 Orthodox
9) Anaphora of St. Athanasius
10) Anaphora of St.Basil
11) Anaphora of St. Gregory Nazianzen
12) Anaphora of St.Epiphanius
13) Anaphora of St. Cyril
14) Anaphora of James Serug (The complete Ethiopian Liturgy)

In each of these Anaphoras the words of Institution differ. The words of Institution in the “Liturgy Of the Apostles” are” take, eat, this bread is my body, which is broken for you for the forgiveness of sins “ –” take, drink, this cup is my blood, which is shed for you and for many”. The consecration is called MELAWAT, i.e. “change”.

These are 14 Anaphoras ascribed to various saints, but only one is normally used, the alternate once being only for rare occasions. The normally one, that of the Twelve Apostles, is fundamentally identical with the Coptic Liturgy Of St. Cyril, although much more developed. The majority of these Anaphoras are comparatively late, apparently coming after the tenth century. The Anaphora of our Lord is used on the feasts of our Lord and on Mount Tabor; our Lady on the feasts of our Lady Mary, Gabriel and Dacesius; John the Son of Thunder on the feasts of St. John the Evangelist, St. Stephen, St. George, all Martyrs and Christmas; John Chrysostom on vigil of Passover, Day of Our Saviour, Feast of Cross, feast of John Chrysostom; Athanasius on Christian Sabbath; Epiphanius on Baptism day, the month of Rains; the 318 Nicean Fathers on feasts of Kana of Galilee, Gena, 24 Heavenly Priests; Gregory Nazianzen, Hosanna Feast and at Passion; Dioscorus on Ascension, Pentecost; Basil, feasts of all Patriarchs and Bishops; Cyril, on feast of Cyril the Patriarch and feasts of all the righteous and prophets; James Serug, on St. Michael and St. Gabriel, all Angels.

Liturgy is celebrated daily. In addition to the celebrant (main priest) and at least one other priest, the presence of three deacons is required. The Ethiopic Liturgy is an expansion of the version of St. Mark, the rite used by the Coptic Church in Egypt. It is divided into pre-anaphora and anaphora. Anaphora corresponds to CANON of the Mass in the Western Churches. While the Western Churches has one anaphora (canon), the canon of the Mass with its Preface, there are fourteen Anaphoras in the Ethiopian Liturgy. However, the anaphora of the Twelve Apostles in the standard form in the Ethiopian Church and the others are used on special days.
1 Comments